Ethiotelecom Logo

ቴሌግራም እና ኢትዮጲያ


ቴሌግራም እና ኢትዮጲያ

       ቴሌግራም በአለምአቀፍ ደረጃ ተደራሽ የሆነ ፍሪሚየም፣ በሁሉም አይነት ፕላትፎርሞች ላይ መስራት የሚችል፣ በኢንተርኔት ክላዉድ ላይ የተመሰረተ ፈጣን መልእክት አገልግሎት ነው። አገልግሎቱ አማራጭ ደህንነታቸዉ የተጠበቀ ቻቶች እና የቪዲዮ ጥሪዎች፣ የስልክ ድምፅ ልዉዉጦችን፣ ፋይል መጋራት እና ሌሎች በርካታ ባህሪያትን ያቀርባል። ለአይኦኤስ ስልክ እ.ኤ.አ በ14 ነሃሴ 2013 እና አንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚዎች በጥቅምት 20 2013 ተጀመረ።

      የቴሊግራም መስራቾች ወንድማማቾቹ ፓቪል እና ኒኮላይ ድሮቭ ናቸዉ፡፡ አሁን በዋናነት ካምፓኒዉን የስራ አስፈፃሚ በመሆን እያገለገለ የሚገኘዉ ፓቬል ድሮቭ ነዉ፡፡

ቴሌግራምን ከሌሎች ተመሳሳይ አፕሊኬሽን ምን የተሻለ ያደርገዋል ?

  1. ያልተገደበ መረጃ ማከማቻ ማቅረቡ

ቴሊግራም ያለተገደበ የመረጃ ማከማቻ ቋት ለተጠቃሚዎቹ ያቀርባል፡፡ ሁሉም የምንላላከችዉ መልዕክቶች ፤ ምስሎች ፤ ቪዲዮዎች ፤ ፋይሎች እና ዶከመንቶች በኢንተርኔት አማካኝነት ክላዉድ ሰርቨር ላይ ይከማቻሉ፡፡ከተለያዩ አይነት መጠቀሚያ አፕሊኬእሽኖች የፈለጉትን ያህል ጊዜ መግባት እና መዉጣት ይችላሉ ፤ በዚህ ሂደት ዉስጥ ግዜ ምንም አይነት መረጃ አይጠፋብንም፡፡ በምን ያህል አፕሊኬሽኖች እየተጠቀምን እንደሆን ዝርዝር መረጃዎችን መመልከት እንችላለን፡፡

ያስቀምጥናቸዉን ፋይሎች ከየትኛዉም ቦታ ሆነን ዳዉንሎድ ማድረግ እና መጠቀም እንችላለን፡፡ በአንድጊዜም እስከ 2 ጊጋ ባይት ሳይዝ ያለዉ ፋይል መጠቀም እንችላለን፡፡

2. የሚዲያ ኮምፕረሽን

ተጠቃሚዎች የአንድን ምስል ድምፅ ወይም ቪዲዮ ኦርጂናሉን መላላክ ያስችለናል በተጨማሪም ፋይሎቹ ኮምፕረስ ወይም የያዙት ፋይል የማጠራቀሚያ አቅም ተቀንሶ መላክ ያስችለናል፡፡

3. የቡድን አባላት ብዛት መጠን

ቴሌግራም በሀገራችን ተመርጭ ከሆነባቸዉ ምክንያቶች አንዱ ግሩፖች እስክ 200 000 ሰዉ እንዲይዙ ማስቻሉ ነዉ፡፡ በአንፃሩ ዋትሳፕ በአንድግሩፕ ከ256 ሰው በላይ አይቻልም፡፡

ለትምህርት ፤ ለዉይይት ፤ እቃዎችን ለመሽጥ እና ተመሳሳይ ጉዳዮች የቴሌግራም ግሩፖች በጣም ጠቃሚ ናቸዉ፡፡

4. በ@ የሚጀምር የተጠቃሚ መለያ

በቴሌግራም ከሰዎች ጋር ለመግባባት ግዴታ ስልክቁጥራቸው ሊኖረን አይገባም፡፡ በ@ የሚጀምር የተጠቃሚዎች መለያ መግባባት እንችላለን፡፡ ይህም የተጠቃሚዎችን ስልክ እና ተያያዥ መረጃዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ያስችለናል፡፡ የተለያዩ ግሩፖች እና ቻናሎችም ላይ ስልካችንን ሳናጋራ በመለያችን መቀላቀል ያስችለናል፡፡

5. ቻናሎች

ቻናሎች የቴሌግራም እጅግ ተመራጭ ገፅታዎች ናቸው፡፡ ቻናሎች ከግሩፖች ጋር ብዙ ተመሳሳይነት ቢኖራቸዉም ዋናው ግን በአባላት ቁጥር አለመወሰናቸው ነዉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የቻናሉ ባለቤት ማን መሳተፍ እንደሚችል እና መፃፍ እንደሚችል የመወሰን መብት አለው፡፡

6. በብዙ ፕላትፎርም መስራቱ

ቴሊግራም በሁሉም የቴክኖሎጂ ዉጤቶች መጠቀም እንድንችል ተደርጎ ነዉ የተዘጋጀዉ፡፡ በአንድሮይድ ፤ አይፎን እና ዊንዶውስ ስልኮች በሞባይል አፕሊኬሽን እንዲሁም በኮምፒዉተሮች በ ዊንዶዉስ ፤ ማክ እና ሊነክስ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ላይ በዴስክቶፕ አሊኬሸ   እና ብሮዉዘር አማካኝነት መጠቀም ያስችለናል፡፡

7. ሰክሬት ቻት

ሰክሬት ቻት ራሱን በራሱ ማጥፋት የሚችል ከላኪ እስከተጠባቂ ደህነንቱ የተረጋገጠ የመልዕክት ልዉዉጥ ነዉ፡፡ ይህ ቻት ራሱን በራሱ የሚያጠፋ ሰልፍ ዲስትራክተር ታይመር አለዉ፡፡  ስክሪንሾት ማድረግ አይቻልም ፤ ለማድረክ ከሞከርም ለሌላኛዉ አካል ማስታወቂያ ይልካል፡፡ እስካሁን ባሉት ሁኒታዎች ይሄንን የቴሊግራም ገፅታ  ሃክ ማድረግ አልተቻለም፡፡

8. ቦቶች

ቦቶች አንዱ የቴሌግራም ገፅታዎች ናቸዉ፡፡ እነዚህ ቦት ፕሮግራሞች በተወሰነ መሉ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እና ማሽን ለርኒግን አጣምረዉ የያዙ ናቸዉ፡፡ በሰጠናቸዉ ሃላፊነት መልኩ ግሩፕን ከምቆጣጠር ጀምሮ እጅግ ብዙ ስራዎችን መከወን ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ኢሜጅ ቦት ስያሜ ስጥተነዉ ከኢንተርኔት ላይ ምስሎችን ፈልጎ ማምጣት ይችላል፡፡
 

9. የድምፅ እና ቭዲዮ ጥሪዎች

አዳዲሶቹ የቴሌግራም ስሪቶች ሁለቱንም የድምጽ እና የቪዲዮ ጥሪዎችን አካትቷል፡፡ በተጨማሪም መልዕክቶችን ቀጠሮ ማስያዝ እና ስብሰባዎች ላይ ያለንን የኮምፒዉተር ስክሪን የምናጋራበት ስክሪን ሼር ገፅታዎችን አካትቷል፡፡


Reviews

  Mikiyas Ephrem
 Oct 17, 2022
  "Arif"

Post Comment